የብላታ መርስዔ ኀዘን አማርኛ ስነ ጽሁፍ ሽልማት
የብላታ መርስዔ ኀዘን መታሰቢያ ድርጅት በአሜሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው። ይሀ ድርጅት ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ለአማርኛ ቋንቋ እና ስነ ጽሁፍ ያበረከቱትን ልዩ አስተዋጽዖ ለመዘከር እና ወጣት አማርኛ ፀሀፍያንን ለማበረታታት “የብላታ መርስዔ ኀዘን አማርኛ ስነ ጽሁፍ ሽልማትን” አዘጋጅቷል። በዚህ አመት በጥር ወር ከሚከናወነው ዝግጅት ጀምሮ በየአመቱ ሊካሄድ የታቀደው የሽልማት ስነ ስረአት ሁለት ውድድሮችን የካትታል፦
1. የስነ ጽሁፍ ሊቅ ሽልማት
ይህ የሽልማት ዘርፍ ለአማርኛ ስነ ጽሁፍ የሚመሰገን አስተዋጽዖ ላደረገ እድሜው ከአርባ አመት በታች ለሆነ ወጣት ፀሀፊ የሚሰጥ ነው። ይህም ተሸላሚ ሀያ ሽህ (20000) የኢትዮዽያ ብር ያሽለማል።
2. የአጭር ስነ ጽሁፍ ሸልማት
ይህ የሽልማት ዘርፍ የሚበረከተው በኢትዮዽያ ውስጥ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ለሚማሩ የቅድመ ምረቃ ወይም የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆን፣ በውድድሩ አንደኛ የሚወጣው ተማሪ አስር ሽህ (10000) የኢትዮዽያ ብር ሁለተኛ የሚወጣው ደግሞ አምስት ሽህ (5000) የኢትዮዽያ ብር ይሸለማል።