የብላታ መርስዔ ኀዘን አማርኛ ስነ ጽሁፍ ሽልማት ውድድርን የተመለከቱ
ደንቦቸ እና ህጎቸ
ለውድድሩ ብቁ የሆኑትን ተወዳዳሪዎች እና በጥቆማ ወደውድድሩ የሚገቡትን ተሳታፊዎች በግልጽ ለመለየት፣ የሽልማቱ አዘጋጆች ሶስት ዳኞችን ይመርጣሉ ።ዳኞቹም የተወዳዳሪዎችን ስራ ገምግመው አሸናፊዎቹን ያሳውቃሉ። የዳኞቹ ውሳኔ አይቀየርም ለድርድርም አይቀርብም። ሁለቱን የ ሽልማት ዘርፎች በተመለከተ የወጡ ህጎቸ በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
1. የስነ ጽሁፍ ሊቅ ሽልማትን በተመለከተ፡
ለስነ ጽሁፍ ሊቅ ሽልማት እጩ ሆነው የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎቸ በስማቸው የታተሙ እና ምስጋናን ያተረፉ የስነ ጽሁፍ ስራዎች ሊኖራቸው ይገባል ። ወደውድድሩ ለመግባት በአንባብያን ሊጠቆሙ ወይንም እራሳቸውን ሊጠቁሙ ይችላሉ። እድሜው ከ 40 አመት በለይ የሆነ ጸሀፊ በውድድሩ መሳተፍ አይችልም።
2. የአጭር ስነ ጽሁፍ ሸልማትን በተመለከተ፡
ለአጭር ስነ ጽሁፍ ሸልማት እጩ ሆነው የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎቸ ኢትዮዽያ ውስጥ በሚገኝ ዩንቨርስቲወዎች ውስጥ የቅድመ ምረቃ ወይም የድህረ ምረቃ ተማሪ መሆን አለባቸው ። በውድድሩ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተማሪዎች እራሳቸው በመረጡት ርዕስ ላይ ከ 10 ገጽ ያልበለጠ የመወዳደሪያ ስነ ጽሁፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።