የብላታ መርስዔ ኀዘን አማርኛ ስነ ጽሁፍ ሽልማት
የብላታ መርስዔ ኀዘን መታሰቢያ ድርጅት በአሜሪካ ውስጥ የሚንቀሳቀስ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም ነው። ይሀ ድርጅት ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ለአማርኛ ቋንቋ እና ስነ ጽሁፍ ያበረከቱትን ልዩ አስተዋጾ ለመዘከር እና ወጣት አማርኛ ፀሀፍያንን ለማበረታታት “የብላታ መርስዔ ኀዘን አማርኛ ስነ ጽሁፍ ሽልማትን” አዘጋጅቷል። በዚህ አመት በጥር ወር ከሚዘጋጀው ዝግጅት ጀምሮ በየ ሁለት አመቱ ሊካሄድ የታቀደው የሽልማት ስነ ስረአት ሁለት ውድድሮችን የካትታል፦
1. የስነ ጽሁፍ ሊቅ ሽልማት
ይህ የሽልማት ዘርፍ ለአማርኛ ስነ ጽሁፍ የሚመሰገን አስተዋጾ ላደረገ ከአርባ አመት በታች ለሆነ ወጣት ፀሀፊ የሚሰጥ ነው። ይህም ተሸላሚ 20000 የኢትዮዽያ ብር ያገኛል።
2. የአጭር ስነ ጽሁፍ ሸልማት
ይህ የሽልማት ዘርፍ የሚበረከተው በኢትዮዽያ ውስጥ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች ለሚማሩ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ሲሆን፣ በውድድሩ አንደኛ ለሚወጣው ተማሪ 10000 የኢትዮዽያ ብር ሁለተኛ ለሚወጣው ደግሞ 5000 የኢትዮዽያ ብር ይሰጣል።